ተአምርዎ የእኛ 

ተልእኮ ነው!

ተአምርዎ የእኛ ተልእኮ ነው!

ተልዕኳችን ሁሉም የአገልግሎታችን ፈላጊዎች ልጅ ወልዶ መሳም እንዲችሉ፣ በከፍተኛ ጥንቃቄ፣ እጅግ ታስቦበት በላቀ የሙያ ደረጃ ጸንሰው የሚወልዱበትን እድል መፍጠር ነው፡፡ በተቋማችን የላቀ የመካንነት ችግር የማስወገድ ህክምና የምንሰጥ ሲሆን አሉ የተባሉ ሙያተኞች በተቋማችን ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው ምቾተዎ ሳይጓደል በስኬት ልጅ ወልዶ ለመሳም ያስችለዎታል፡፡

ኒው ሊፍ የመካንነት ህክምና ማዕከል ራዕዩ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው አገልግሎት ሰጪ የመካንነት ህክምና ማዕከል ሆኖ መገኘት ሲሆን ሴቶች ከመጸነስ አንስቶ ልጅ ወልደው እስኪስሙ ድረስ ያልተቋረጠ ህክምና፣ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እና እንክብካቤ እንሰጣለን፡፡ ተቋማችን ግንባር ቀደም የማኔጅመንት አገልግሎት እና እንክብካቤ በመጠቀም የታካሚ ደህንነት ተጠብቆ በላቀ የሙያ ስነ ምግባር የሚታገዝ የመካንነት ህክምና ይሰጣል፡፡ ታካሚዎቻችን ልጅ ወልደው የሚስሙት በአጋጣሚ ሳይሆን በታቀደ እና በታሰበበት መልኩ ነው፡፡

ኒው ሊፍ የመካንነት ህክምና የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ግንባር ቀደም እና የፈጠራ እገዛ የሚደረግላቸው አሉ የተባሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ የሚውሉበት ነው፡፡ ሙያዊ እንክብካቤ እና የታካሚዎች የግል ክትትል እና እገዛ የሚሰጡት ባለሙያዎቻችን ታካሚዎች ጤናማ ልጅ ወልደው አይናቸውን በአይናቸው ለማየት የሚችሉበትን ደረጃ የላቀ ያደርጉታል፡፡

ተቋማችንን ለምን ይመርጡታል?

ቀጠሮ ይያዙ

ቤተሰቦች ልጅ ወልደው መሳም እንዲችሉ ማንኛውንም አማራጭ እናቀርባለን

ለመልእክትዎ እናመሰናለን ፡፡ ተልኳል ፡፡
መልእክትዎን ለመላክ ስህተት ነበር። እባክዎ ቆየት ብለው ይሞክሩ፡፡ትዎን ለመላክ ስህተት ነበር። እባክዎ ቆየት ብለው ይሞክሩ፡፡